am_tn/mic/06/09.md

2.1 KiB

የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጣራል

ድምፅ ሰውየውን ሲወክል ከተማ ደግሞ በውስጡ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል”።

አሁን እንኳን ጥበብ ለስምህ ዕውቅና ትሰጣለች

ጥበብ እንደ ሰው ተነግሮላታል፣ በፈሊጣዊ አነጋገር ጥበበኛን ሰው ያመለክታል። እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል ስለ ሰውየው ስለ ራሱና ሰዎች ስለ ሰውየውና ስለ ሥልጣኑ የሚያስቡትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ጥበበኛው ሰው ይፈራሃል” ወይም “ጥበበኛ ሰው አንተ መልካም መሆንህን ያውቃል፣ ይታዘዝሃልም”።

በትሩንና በስፍራው ያስቀመጠውን እርሱን ልብ በሉ

እዚህ ጋ “በትር” እግዚአብሔር “በስፍራው ያስቀመጠው” እና የራሱን ሕዝብ የሚቀጣበትን የጠላትን ሰራዊት ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አታላዮች በሆኑ በክፉዎች ቤት ውስጥ ባለጸግነት አለ

በማታለል የተገኘ ባለጸግነት ሰዎች በማታለል ተግባር ያገኙትን ባለጸግነት የሚያሳይ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። “ክፉው” የሚለው ቃል ክፉዎች ሰዎችን ያመለክታል። ቤቶች አንድ ሰው የራሱ ንብረት የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ የሚያመልክት ምሳሌ ነው። አ.ት፡ “ክፉዎች ሰዎች ባለጸግነትን ለማግኘት የማታለልን ተግባር ፈጽመዋል”።

ሐሰተኛ መለኪያ

ሰዎች ብልጽግናቸውን ለማብዛት የሚገበያዩአቸውን ሌሎች ሰዎች በሚዛን በማጭበርበር የሚጠቀሙበት ትክክለኛ ያልሆነ መስፈሪያ ነው።