am_tn/mic/06/03.md

2.5 KiB

ሕዝቤ ሆይ፣ ምን አድርጌአችኋለሁ? ያደከምኳችሁ በምንድነው? መስክሩብኝ!

እግዚአብሔር መልካም አምላክ ስለመሆኑና ሕዝቡ እርሱን ማምለካቸውን እንዲያቆሙ የሚያስደርግ ምንም ነገር እንዳላደረገ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “ሕዝቤ ሆይ፣ እኔ ለእናንተ መልካም ነበርኩኝ። በእኔ ምክንያት የምትደክሙበትን ምንም ነገር አላደረግሁም። እንዳደረግሁ ካሰባችሁ አሁን መስክሩብኝ”።

ለእናንተ … አደከምኳችሁ? መስክሩ … አመጣዃችሁ … አዳንኳችሁ … ማርያምን ለእናንተ … አስቡ … ሄዳችሁ … ታውቁ ዘንድ

ሚክያስ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለሕዝቡ ይናገራል፤ ስለዚህ ትዕዛዞቹ ሁሉና “አንተ” የሚሉት ሁሉ ተባዕታዊ ነጠላ ቁጥር ናቸው።

የባርነት ቤት

ቤት አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ የሚኖርበት ስፍራ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። የንገር ስም የሆነው “ባርነት” “ባሪያዎች ልትሆኑ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ለረጅም ጊዜ ባሪያዎች ሆናችሁ የኖራችሁበት ስፍራ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ባላቅ የመከረውን

“ባላቅ እናንተን ለመጉዳት ያቀደውን”

በለዓም እንዴት … እንደ መለሰለት

  1. በለዓም ባላቅ በጠራው ጊዜ በመምጣቱ ለባላቅ ታዞአል። አ.ት፡ “በለዓም ባላቅ እንዲያደርግ የጠየቀውን … እንዴት እንዳደረገ” ወይም 2) ባላቅ እንዳዘዘው እስራኤላውያንን በመርገም ፈንታ ለምን እንደባረካቸው በለዓም ለባላቅ አብራራለት። አ.ት፡ “በለዓም ለባላቅ የነገረውን” ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች ናቸው።

ቢዖር

ይህ የበለዓም አባት ስም ነው።

ሰጢም

ይህ በሞዓብ የሚገኝ የቦታ ስም ነው።

ስለዚህ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራዎች ታውቁ ዘንድ

እግዚአብሔር በገዛ ስሙ ወደ ራሱ ያመለክታል። አ.ት፡ “እኔ እግዚአብሔር ያደረግሁላችሁን የጽድቅ ነገሮች ታስታውሱ ዘንድ”።