am_tn/mic/06/01.md

2.0 KiB

መዋቅሩና አቀራረቡ

ይህ ምዕራፍ የተጻፈው እንደ ፍርድ ቤት ጉዳይ ወይም እግዚአብሔር በራሱ ሕዝብ ላይ ሙግት እንዳለው ሆኖ ነው።

በሙግቱ ውስጥ ያሉት ስሞች በዚህ ምዕራፍ ለመተርጎም አስቸጋሪ ከሚሆኑት ውስጥ ናቸው

ሙሴ፣ አሮንና ማርያም በእስራኤል ላይ ለእግዚአብሔር ምስክር ሆነው ተጠቅሰዋል። አክዓብና ዖምሪ እግዚአብሔርን እንዳልተከተሉ ክፉ ነገሥታት ሆነው ተጠቅሰዋል። ለሙሴ ሕግ መታዘዝ ለሕጉ ካለመታዘዝ ጋር ተነጻጽሯል።

እንግዲህ ስሙ … የእግዚአብሔርን ሙግት ስሙ

ሚክያስ ሊሰሙት ይችሉ ይመስል ለተራሮች ሲናገር የሚናገረው ለእስራኤል ሕዝብ ነው፤ ስለዚህ በሁለቱም አገላለጽ “ስሙ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው።

ተነሥ … አቅርብ … ድምፅህ …

ሚክያስ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፤ ስለዚህ ትዕዛዞቹና “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው።

ተነሥና በተራሮቹ ፊት ነገርህን አቅርብ፤ ኮረብቶቹም ድምፅህን ይስሙ

እግዚአብሔር በፍርድ ቤት እንዳለና ተራሮችና ኮረብቶች ፈራጆቹ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል። የእስራኤል ሕዝብ ያደረጉትን ለምን እንዳደረጉ ለዳኞቹ እንዲናገሩ ያዛቸዋል።

ተራሮቹ … ኮረብቶቹ … የጸኑት የምድር መሠረቶች

ሚክያስ ሰዎች እንደሆኑ ቆጥሮ ለእነዚህ ነገሮች ይናገራል። ሚክያስ ተራሮችን፣ ኮረብቶችንና የምድርን መሠረቶች በሕዝቡ ጣዖት አምላኪነት ላይ ዘላለማዊ ምስክር አድርጎ ያቀርባቸዋል።