am_tn/mic/05/08.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እግዚአብሔር ሕዝቡን በጦርነት ከቀጣቸው በኋላ በሕይወት ያሉት እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ፈጽመው ድል እንደሚያደርጉና እንደሚገዟቸው እግዚአብሔር ተስፋ ይሰጣል።

የያዕቆብ ትሩፍ

ከጦርነቱ የሚተርፉ የያዕቆብ ተወላጆች

በአገራት መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ሲሆን “የያዕቆብ ትሩፍ” በብዙ የተለያዩ አገሮች እንደሚኖሩ አጽንዖት ይሰጣሉ።

በጫካ እንስሶች መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበግ መንጋም መካከል እንዳለ የአንበሳ ደቦል

አናብስት በጫካ የሚኖረውን የትኛውንም እንስሳ መግደልና መብላት ይችላሉ፣ በጎችንም በቀላሉ ይገድላሉ። አ.ት፡ “እንደ ተናካሽ የዱር እንስሳት፣ ምስኪን ከብቶችን እንደሚገድሉ የዱር እንስሶች”

በመካከላቸው በሚሄድበት ጊዜ

የአንበሳ ደቦል በበግ መንጋ መካከል በሚሄድበት ጊዜ

እላያቸው ላይ ይከመርባቸውና ይዘነጣጥላቸዋል

“ይዘልባቸውና ይጥላቸዋል፣ ከዚያም ይዘነጣጥላቸዋል”

እጅህ … ጠላቶችህ

ጸሐፊው የሚናገረው እግዚአብሔርን ነው፤ በመሆኑም “አንተ” የተሰኙት ሁለቱም ተባዕት ነጠላ ቁጥር ናቸው።

እጅህ በጠላቶችህ ላይ ይነሣል

እጅ በፈሊጣዊ አነጋገር ለመሥራት ያለውን ኃይል ገላጭ ነው ወይም የሰውን ሁለንተና የሚወክል ምልክት ነው። እጅን ማንሣት ኃይልን መግለጥ ነው። አ.ት፡ “ጠላቶችህን ሙሉ በሙሉ ድል ታደርጋቸዋለህ”።

ያጠፋቸዋል

እጅ የሰውን ሁለንተና የሚወክል ምልክት ነው። አ.ት፡ “ታጠፋቸዋለህ”