am_tn/mic/05/06.md

2.0 KiB

የአሥራውያንን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩድንም ምድር በበሩ ላይ በእረኝነት ይጠብቃሉ

ሰይፍ በጦርነት ውስጥ ለመግደያነት በፈሊጣዊነት ተነግሯል። እዚህ ጋ እስራኤላውያን በጎችን ከመጠበቅ ይልቅ ያረዷቸው በሚመስል መልኩ በአሦራውያን ላይ ገዢ መሆናቸው በምጸት ተነግሯል። የአሦር ምድር በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። የከተሞቹ በሮች ሕጋዊ ንግድ የሚካሄድባቸው ስፍራዎች ነበሩ። አ.ት፡ “የአሦርን ሕዝብ ይወጋሉ፣ የናምሩድን ምድር ክተሞችም ይገዛሉ”። ጦርነት

የናምሩድ ምድርም

“በእረኝነት ይጠብቃሉ” የሚሉትን ቃላት ከዐረፍተ ነገሩ መነሻ መረዳት ይቻላል። ሊደጋገሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “የናምሩድን ምድር በእረኝነት ይጠብቃሉ”።

የናምሩድ ምድር

ይህ የአሦር ምድር ሌላው ስሙ ነው። ናምሩድ አደን ያድን የነበረ የቀድሞ ገዢ ነበር። ተርጓሚዎች ይህንን የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይኖርባቸው ይሆናል፤ “ ‘ናምሩድ’ የሚለው ስም ትርጉም ‘ዓመፅ’ ማለት ነው”።

ያድናል

ገዢው ያድናል

ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ጠል፣ በሣሩ ላይ እንደሚወርድ ካፊያ

ጠልና ዝናብ ምድሪቱን በማረስረስ አንዳንድ ነገሮች እንዲበቅሉ ያደርጋሉ። እስራኤላውያን በመካከላቸው የሚኖሩባቸው ሕዝቦች በሰላም እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል።

ሰውን የማይጠብቅ ሣር፣ የሰው ልጆችንም አይጠብቁም

“ሣር ሰውን ወይም የሰው ልጆችን አይጠብቅም”፤ ጠልንና ዝናብን የሚያርከፈክፍ እግዚአብሔር ብቻ ነው።