am_tn/mic/05/04.md

1.7 KiB

እርሱ በእግዚአብሔር ኃይል ይቆማል፣ መንጋውንም ይጠብቃል

በጎቹን የሚመግብና የሚጠብቅ እረኛ ለእስራኤል ሕዝብ የሚያስፈልጋቸውን የሚያቀርበውንና የሚጠብቃቸውን ገዢ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡን እንዲመራለት እግዚአብሔር ኃይልን ይሰጠዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ

የሰውየው ስም ስላለው ሥልጣን ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አምላኩ እግዚአብሔር እንዲገዛ ሥልጣንን ስለሰጠው ሰዎች ያከብሩታል”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ ይኖራሉ

የእስራኤል ሕዝብ ይኖራሉ

ይኖራሉ

“በሰላም ይኖራሉ”

እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናል

በየአገሩ ያለ ሕዝብ ሁሉ ለእስራኤል ገዢ ክብርን ይሰጠዋል

ሰባት እረኞችንና ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋለን

እዚህ ጋ “እረኞች” የሚለው ቃል በሌላ አነጋገር “ሰዎችን የሚመሩ” ሲሆኑ በፈሊጣዊ አነጋገር “ገዢዎች” ማለት ነው። “ሰባት … እና ስምንት” የሚለው ሐረግ “ከበቂ በላይ” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በቂ፣ ከበቂም እንኳን በላይ የሆኑ መሪዎች” ወይም “በሰዎች ላይ ከበቂ በላይ የሆኑ እረኞችና መሪዎች”