am_tn/mic/05/02.md

2.1 KiB

አንቺ ቤተ ልሔም ኤፍራታ

እግዚአብሔር ለቤተ ልሔም ከተማ ለራሷ በሚናገርበት መልኩ ለይሁዳ ሕዝብ፣ በተለይም ለቤተ ልሔም ሕዝብ ይናገራል።

ኤፍራታ

ይህ ቤተ ልሔም የምትገኝበት አካባቢ ስም ወይም የቤተ ልሔም ሌላኛው ስሟ ወይም ይህችኛዋን ቤተ ልሔም ከሌላው መለያ ይሆን ይሆናል። ቤተ ልሔም ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ ስድስት ማይል ርቀት ላይ ትገኛለች። የንጉሥ ዳዊት የትውልድ መንደር ነበረች። ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይኖርባቸው ይሆናል፤ “ ‘ኤፍራታ’ የሚለው ስም ትርጉም ‘ፍሬአማ መሆን’ ማለት ነው”።

በይሁዳ ጎሳዎች መካከል ታናሽ ብትሆኚም አንድ ከአንቺ የሚወጣ አለ

“በይሁዳ ጎሳዎች ውስጥ ብዙ ሕዝብ ያለው ሌላ ቢኖርም ከሕዝብሽ የሚመጣው አንድ ነው”

ወደ እኔ ይመጣል

እዚህ ጋ “እኔ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል።

ጅማሬው ከጥንት ዘመን፣ ከዘላለም የሆነ

ይህ ከንጉሥ ዳዊት ጥንታዊ ቤተ ሰብ የሚመጣውን ገዢ ያመለክታል። “ከጥንት ዘመን” እና “ከዘላለም” የሚሉት ሐረጎች ትርጉማቸው በመሠረቱ አንድ ሆኖ የቤተ ሰቡ የትውልድ ሐረግ ምን ያህል ረጅም መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ።

ስለዚህ

“የተናገርኩት እውነት ስለሆነ” ወይም “ምክንያቱም በኋላ ይህ ገዢ ይመጣል”

ይተዋቸዋል

የእስራኤልን ሕዝብ ይተዋቸዋል

የምታምጠው እርሷ ልጅ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ

ይህ ገዢው የሚወለድበትን የተወሰነ ጊዜ ያመለክታል።

የቀሩት ወንድሞቹ

በምርኮ ያሉ “የቀሩት የገዢው እስራኤላውያን ጓደኞች”