am_tn/mic/04/13.md

1.5 KiB

የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነሺ ውቂ …ቀንድሽ …ኮቴዎችሽ … ታደቂያቸዋለሽ

“ያንቺ” እና “አንቺ” የተባሉት ሁሉ እንዲሁም ትዕዛዛት “የጽዮንን ሴት ልጅ” የሚያመለክቱ ሲሆኑ ነጠላ ቁጥርና አነስታይ ናቸው።

የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነሺ ውቂ፣ ቀንድሽን ብረት አደርገዋለሁ፣ ኮቴሽንም ነሐስ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ

እግዚአብሔር የጽዮንን ሕዝብ ስንዴ እንደሚወቃ ብርቱ በሬ፣ ጠላቱንም እንደ ስንዴ አድርጎ ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)

ቀንድሽን ብረት አደርገዋለሁ፣ ኮቴሽንም ነሐስ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ

አንባቢህ በሬን ወይም ብረትን ወይም ነሐስን የማያውቅ ከሆነ ዘይቤአዊውን አነጋገር ልትተወው ትችላለህ። አ.ት፡ “ጠላቶችህን ሁሉ ማሸነፍና ማጥፋት እንድትችል አደርግሃለሁ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የግፍ ሀብታቸውን

“ግፍን በማድረግ ያገኙትን ሀብት” ወይም “ከሌሎች ሰዎች የሰረቋቸውን ነገሮች”

ሀብታቸውን

የነገር ስም የሆነው “ሀብት” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የራሳቸው ያደረጓቸው ነገሮች”