am_tn/mic/04/11.md

773 B

የረከሰች ትሁን

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እናርክሳት”።

ዓይኖቻችን በመፈንደቅ ጽዮንን ይዩ

ዐይን የሰውን ሁለንተና የሚወክል ምሳሌ ነው። አ.ት፡ “ጽዮንን በመፈንደቅ እንያት” ወይም “ወራሪዎች ጽዮንን ሲያጠፏት በማየት ደስ ይበለን”።

በዐውድማ ላይ ለመወቃት እንደተዘጋጀ የእህል ክምር አንድ ላይ ሰብስቧቸዋል

ጸሐፊው እግዚአብሔር የእህሉን ክምር ዐውድማው ላይ እንዳደረገና ሊወቃው እንደተዘጋጀ ገበሬ አገሮችን ለማጥፋት መዘጋጀቱን ይናገራል።