am_tn/mic/04/09.md

2.4 KiB

አሁን ድምፅህን ከፍ አድርገህ የምትጮኸው ለምንድነው?

ሚክያስ ሕዝቡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ለምን እንዲህ ባለ መንገድ እንደሚናገር እንዲያስቡ ለማድረግ በመሞከር በሕዝቡ ላይ ያላግጥባቸዋል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ምን ያህል እንደምትጮኹ ተመልከቱ” ወይም “በኃይል የምትጮኹት ስለምን እንደሆነ በጥንቃቄ አስቡ”።

በመካከላችሁ ንጉሥ የለም? አማካሪዎቻችሁ ሞተዋል? እንደምታምጥ ሴት ሕመም የያዛችሁ ለዚህ ነው?

ሚክያስ በሕዝቡ ላይ ማላገጡን ቀጥሏል። እነዚህ ጥያቄዎች እንደ መግለጫዎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ንጉሥ አላችሁ፣ ነገር ግን ምንም አይጠቅማችሁም። ጥበበኞቻችሁ ገና በሕይወት አሉ፣ ነገር ግን ምንም የሚነግሯችሁ ጥበብ የላቸውም። ለዚህ ነው ልጅ እንደምትወልድ ሴት ድምፃችሁን አውጥታችሁ የምታለቅሱት”።

እንደምታምጥ ሴት የታመማችሁት

ሚክያስ ጠላት ከከተማቸው እንዲወጡ ሲያስገድዳቸው ሕዝቡ የሚገጥማቸውን ሥቃይ አንዲት ሴት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ከሚሰማት ሕመም ጋር ያነጻጽረዋል።

በዚያ ትድናላችሁ። በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል

እግዚአብሔር እንደሚያደርግ የተናገረውን እንደሚያደርግ አጽንዖት ለመስጠት በገቢራዊና በኢገቢራዊ ድምፅ በሁለቱም ተመሳሳዩን ነገር ይናገራል። ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል። በዚያ እርሱ ያድናችኋል”።

ከጠላቶቻችሁ እጅ

“እጅ” ለሚለው ቃል የሚከተሉት ተስማሚ ትርጉሞች ናቸው፣ 1) እጅ ለሚሠራበት ኃይል ፈሊጣዊ አነጋገር ይሆን ይሆናል፣ አ.ት፡ “የጠላቶቻችሁ ኃይል” ወይም 2) ስለ ሰው ምሳሌ ይሆን ይሆናል። አ.ት፡ “ጠላቶቻችሁ”።