am_tn/mic/04/06.md

3.2 KiB

በዚያን ቀን

“በዚያን ጊዜ” ወይም “እነዚያን ነገሮች በማደርግበት ጊዜ”፤ እነዚህ ቃላት “የመጨረሻዎቹን ቀናት” ያመለክታሉ (ሚክያስ 4፡1)። “ቀን” የሚለው ቃል የተወሰኑ ቀናትን ወይም ዓመታትን እንኳን ሊያመለክት ይችላል።

አንካሳው

ይህ በትክክል መራመድ የማይችሉትን ያመለክታል። አንካሳ መሆን የትኛውንም ዓይነት የአካል ጉዳተኝነት የሚያሳይ ምሳሌ ነው።

የተጣሉትን እሰበስባለሁ

“ከኢየሩሳሌም ያስወጣኋቸውን እሰበስባቸዋለሁ”

ተሰደው የወጡትን ወደ ብርቱ ሕዝብ

“እመልሳለሁ” የሚለውን ቃል ቀድም ብሎ ካለው ሐረግ መረዳት ይቻላል። ሊደጋገሙ ይችላሉ። “ተሰደው የወጡትን” የሚለው ሐረግ በገቢራዊ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አሳድጄ ያስወጣኋቸውን ወደ ብርቱ ሕዝብነት እመልሳቸዋለሁ” ወይም “በግድ ያባረርኳቸውን ብርቱ ሕዝብ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ”።

አንተን የመንጋውን መጠበቂያ ማማ፣ የጽዮን ሴት ልጅ ኮረብታ፣ ለአንተ የቀድሞ ግዛትህ ይመለስልሃል

ሚክያስ ይሰማው ይመስል ለቤተ መቅደሱ ተራራ በሚናገርበት ጊዜ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገሩ ነው። ሚክያስ መልዕክቱን ለሕዝቡ ማድረሱን ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “የቤተ መቅደሱን ተራራ በሚመለከት፣ እግዚአብሔር እናንተን የሚመለከትበት ስፍራ፣ በጎቹ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ስለ ቀድሞ ግዛቱ የሚመኩበት ስፍራ ይመለሳል”።

ለመንጋው የመጠበቂያ ማማ

በመጠበቂያ ማማው ላይ ሆኖ መንጋውን እንደሚጠብቅ እረኛ የኢየሩሳሌም ሕዝብ በዙሪያቸው የሚኖሩትን ሌሎች ሕዝቦች እንደሚጠብቁ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የጽዮን ሴት ልጅ … የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ

በስፍራው የሚኖሩ ሰዎች ስፍራው እንደ እናት፣ እነርሱ እንደ ሴት ልጆች እንደሆኑ ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “በጽዮን የሚኖሩ ሰዎች … በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኮረብታ

አንዳንድ የዘመናችን ትርጉሞች ይህንን የዕብራይስጥ ቃል “ትልቅ ምሽግ” ወይም “ጠንካራ ምሽግ” ማለት እንደሆነ ይረዳሉ።

ለአንተ፣ የቀድሞ ግዛትህ ይመለስልሃል

የነገር ስም የሆነው “ግዛት” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ቀድሞ ታደርግ እንደነበረው አገሮችን ትገዛለህ” ወይም “ቀድሞ እንዳደረግኸው አገራቱን እንድትገዛ አደርግሃለሁ”።