am_tn/mic/04/01.md

1.8 KiB

ተራሮቹ … በሌሎች ተራሮች

እግዚአብሔር የቤተ መቅደሱን ተራራ ከሌሎች ተራሮችና ኮረብቶች ሁሉ ማላቁ ቤተ መቅደሱን በምድር ላይ እጅግ አስፈላጊ ቦታ ስለ ማድረጉ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔር ቤት ተራራ ይመሠረታል

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱ የሚገነባበትን ተራራ ይመሰርታል” ወይም “እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱ ታላቅ ሆኖ የሚገነባበትን ተራራ ይሠራል”።

በሌሎች ተራሮች ላይ

የጽዮን ተራራ ከተራሮች ሁሉ እጅግ አስፈላጊው ይሆናል። በተጨማሪም ይህ ተራራ በሚዋሰንበት አካባቢ ብቻ ሳይሆን በዓለም ከፍተኛው ተራራ ይሆናል ማለት ሊሆን ይችላል።

ከኮረብቶች በላይ ከፍ ይላል

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከኮረብቶች በላይ ከፍ ያደርገዋል” ወይም “እግዚአብሔር ከኮረብቶች ይልቅ ያልቀዋል”።

ሕዝቦች ወደ እርሱ ይጎርፋሉ

ምንጭ ከተለያየ አቅጣጫ ወደ አንድ ስፍራ ባለማቋረጥ ይጎርፋል። ብዙ ሕዝቦች ከተለያየ አቅጣጫ ወደ ቤተ መቅደሱ ተራራ ይመጣሉ። አ.ት፡ “የአገራቱ ሕዝቦች እንደ ምንጭ ወደ እርሱ ይጎርፋሉ” ወይም “የአገራቱ ሕዝቦች ወደ እርሱ ይሄዳሉ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)