am_tn/mic/03/12.md

1.2 KiB

በእናንተ ምክንያት

እዚህ ጋ “እናንተ” የሚያመለክተው ካህናቱን፣ ነቢያቱንና መሪዎቹን ነው (ሚክያስ 3፡11)።

ጽዮን የታረሰ እርሻ ትሆናለች … የመቅደሱም ኮረብታ የቁጥቋጦ ዋሻ ይሆናል

“ጽዮን” እና “የመቅደሱ ኮረብታ” የሚያመለክቱት አንዱን ስፍራ ነው። ገበሬ እርሻ በሚያርስበት ጊዜ ዐፈሩን ይገለብጠዋል፣ በዚያ የበቀሉትን እጽዋት ሥር ሁሉ ይነቅላል። የቁጥቋጦ ዋሻ ለምንም በማይጠቅም በችፍግ የተሞላ ነው። እነዚህ ሁለት ዘይቤአዊ አነጋገሮች በተመሳሳይ ጊዜ ቃል በቃል እውነት ሊሆኑ አይችሉም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የመቅደሱን አካባቢ ፈጽመው እንዲያጠፉ ለወራሪዎቹ እንደሚፈቅድላቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የታረሰው መሬት

“ገበሬ ያረሰው መሬት”

የቁጥቋጦ ዋሻ

ትናንሽ እንጨትነት ያላቸው እጽዋት የሚበቅሉበት አካባቢ ነው።