am_tn/mic/03/09.md

2.3 KiB

የያዕቆብ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተ ሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። በዚህ ጉዳይ ቃሉ የያዕቆብን ዘሮች ያመለክታል። አ.ት፡ “የያዕቆብ ዘሮች”።

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የለሚኖሩትን ቤተ ሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። በዚህ ጉዳይ ቃሉ የእስራኤል ሕዝብ የሆነውን የእስራኤልን ዘር ያመለክታል። አ.ት፡ “የእስራኤል ዘሮች” ወይም “እናንት እስራኤላውያን”።

መጥላት

ከፍተኛ ጥላቻ

ጽዮንን በደም፣ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ትገነባላችሁ

እዚህ ጋ “ደም” በፈሊጣዊ አነጋገር መግደል ማለት ሲሆን “ጽዮን” እና “ኢየሩሳሌም” በሕንጻ ተመስለዋል። ሚክያስ ባለጸጎች ሰዎችን መግደላቸውና ኃጢአት መሥራታቸውን ይናገራል፤ በሌላ አነጋገር ድርጊቶቻቸው ሰዎች ቤቶችን ለመሥራት የሚጠቀሙባቸውን ጡቦችና እንጨቶች ይመስላሉ። አ.ት፡ “ጽዮንን እና ኢየሩሳሌምን ታላቅ ለማድረግ በምትሠሩበት ጊዜ ትገድላላችሁ፣ ሌሎች የከፉ ኃጢአቶችንም ትሠራላችሁ” ወይም “በጽዮን ስታመልኩ ሳላችሁ ትገድላላችሁ፣ በኢየሩሳሌም ስትበለጽጉ ሳላችሁም ሌሎች ኃጢአቶችን ትሠራላችሁ”። (ዘይቤአዊ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አይደለምን?

መሪዎቹ እግዚአብሔር አብሯቸው እንዳለ አጥብቀው ያምናሉ። ይህ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለ እናውቃለን!” ወይም “ለማድረግ የምንፈልገውን እንድናደርግ እግዚአብሔር እንደሚረዳን እናውቃለን”።

ክፉ

በሚክያስ 1፡12 “አደጋ”ን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።