am_tn/mic/03/08.md

1.5 KiB

እኔ ግን

እዚህ ጋ “እኔ” እውነተኛውን፣ ራሱን ከሐሰተኖች ነቢያት የለየውን ሚክያስን ያመለክታል።

በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልን፣ ፍትሕና ብርታትንም ተሞልቻለሁ

ሚክያስ ራሱን እግዚአብሔር ፈሳሽ እንደሚያፈስበት መያዣ ዕቃ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልን፣ ፍትሕንና ብርታትን ሰጥቶኛል” ወይም “እንድጠነክር፣ ፍትሕ ምን እንደሆነ እንድሰብክና ብርቱ እንድሆን የእግዚአብሔር መንፈስ አስችሎኛል”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለያዕቆብ መተላለፉን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን ለማስታወቅ

እዚህ ጋ “ያዕቆብ” እና “እስራኤል” የያዕቆብን ዘሮች የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። ሚክያስ ሁለቱን ስሞች የሚጠቀመው ዘሮቹ ሁሉ በኃጢአት በደለኞች ስለመሆናቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው። የነገር ስም የሆኑትን “መተላለፍ” እና “ኃጢአት” ግሥ በመጨመር መተርጎም ይቻላል። አ.ት፡ “የያዕቆብ ዘሮች የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መጣሳቸውን ለማስታወቅ፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ኃጢአትን መሥራታቸውን እነግራቸዋለሁ”።