am_tn/mic/02/12.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል። በዚህ ምዕራፍ መጨረሻ እግዚአብሔር ራሱን የሕዝቡ ጠባቂ እረኛ አድርጎ ያሳያል። እርሱ የሚናገረው ምናልባትም በተለይ ከአሦር ተመልሰው በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ነው።

ያዕቆብ፣ እናንተን ሁላችሁንም

ሚክያስ የሚናገረው ለአንዳንድ የያዕቆብ ዝርያዎች ሲሆን “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው።

ሰባሪው መንገዳቸውን ይከፍታል … እግዚአብሔር በራሳቸው ላይ ይሆናል።

ይህ ከተከበበ ከተማ ሕዝቡን እየመራ የሚሄደው ንጉሥ ሥዕል ነው።

የሚክያስ 03 ዋና ነጥቦች ፍትሕ የዚህ ምዕራፍ ዋና ጭብጥ ነው

ፍትሐዊ ያልሆነ ማኅበረ ሰብ እንደ ኃጢአተኛ ይቆጠራል። የሙሴን ሕግ እንደሚቃረን ይቆጠርም ነበር። እነዚህ መንግሥታት ፍትሕ ካልነበራቸው ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ነበሩ ማለት ነው።

አስፈላጊ ምሳሌአዊ አነጋገር በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በዘይቤአዊ አነጋገር ቀርቧል

የሕዝቡ መሪዎች እስራኤላውያኑን እንዴት እንደያዟቸው የሚያሳዩ ጉልህ ሥዕሎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህ ሁኔታዎች እንደ ዘይቤአዊ አነጋገር ካልተወሰዱ ዘበት ሆነው ይቀራሉ።