am_tn/mic/02/03.md

1.8 KiB

X

አንገቶቻችሁን ልታስወጡ ከማትችሉበት እግዚአብሔር ቀንበርን በአንገታቸው ዙሪያ ያደረገ ይመስል ሕዝቡን ስለሚቀጣበት ሁኔታ ይናገራል። አ.ት፡ “ልታመልጡ ከማትችሉበት”።

ስለ አንቺ ይዘፍናሉ “በአንቺ ላይ ለመቀለድ ይዘፍኑብሻል” የሀዘን እንጉርጉሮ አንጎራጉሪ “ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ”። የሚወድዷቸው የሞቱባቸው ይመስል ለማልቀስ ያስመስላሉ።

እኛ እስራኤላውያን . . . ለከዳተኞች ይህ ጠላቶቻቸው በእስራኤላውያን ላይ ለመሳቅና በስቃያቸው ለመሳለቅ የሚዘፍኑት ዘፈን ነው።

ከእኔ እንዴት መንጠቅ ይችላል? የእስራኤል መሪዎች ከድኾች የወሰዱባቸውን መሬት እግዚአብሔር ከእነርሱ ወስዶ ለሌላ ሰው በመስጠቱ በሚሰማቸው መደነቅ ላይ ጠላት ይሳለቃል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ተደርጎ መተርጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከእኔ ለመውሰድ ማሰቡ ስሕተት ነው!”

ስለዚህ፣ እናንተ ባለጸጎች በእግዚአብሔር ጉባዔ ውስጥ መሬት የሚካፈል ትውልድ አይኖራችሁም። አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) ሚክያስ ወደ ፊት ከምርኮ በኋላ የሚመለሱት ተመላሾች ምድሪቱን ስለሚከፋፈሉበት ጊዜ ይመለከታል ወይም 2) እርሱ የሚናገረው በዘመኑ ልማድ መሠረት አንድ ነገድ ወይም ጎሳ ምድራቸውን በማከፋፈል ለግለ ሰቦች ስለሚሰጡበት ጊዜ ነው።