am_tn/mic/01/08.md

2.6 KiB

X

ሚክያስ 1፡8-16 የሚናገረው በይሁዳ ላይ ስለሚሆነው የእግዚአብሔር ፍርድ ነው።

የሀዘን እንጉርጉሮን አንጎራጉራለሁ እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሚክያስን ነው።

የሀዘን እንጉርጉሮን አንጎራጉራለሁ፣ አለቅሳለሁም “የሀዘን እንጉርጉሮ” የሚያመለክተው ውስጣዊውን ሀዘን ሲሆን “ለቅሶ” ደግሞ የሀዘንን ድምፅ በጩኸት የመግለጥን ተግባር ያመለክታል።

ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ ይህ የከፍተኛ ለቅሶና ጉዳት ምልክት ነው። ሌላው አማራጭ ትርጉም “አንድ ሰው ልብሴን የገፈፈኝን ዓይነት ሰው እመስላለሁ፤ ራቁቴን እሆናለሁ”

ራቁት ምናልባት ከወገብ በታች ማገልደም ብቻ ይሆናል

እንደ ቀበሮዎች. . . እንደ ጉጉቶች ቀበሮዎችና ጉጉቶች የሚኖሩት ወና በሆነ ምድር ሲሆን ከፍ ያለው ድምፃቸው ዋይ የሚሉ ወይም የሚያለቅሱ ሰዎችን ድምፅ ይመስላል።

ቁስሏ ሊድን የማይችል ነው እዚህ ጋ “እርሷ” የሚያመለክተው የሰማርያን ከተማ ነው። ይህም የጠላት ሰራዊት በዚያ የሚኖረውን ሕዝብ ከማጥፋት ምንም ነገር ሊገታው አይችልም ማለት ነው።

ወደ ይሁዳ መጥቷል ሚክያስ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ለመፍረድ የላከውን ሰራዊት ለመግለጽ በዘይቤአዊ አነጋገር ተላላፊ በሽታ የሚለውን ይጠቀማል። እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው “ቁስል”ን ሲሆን እርሱም እግዚአብሔር ሰማርያን ለመቅጣት የሚጠቀምበት ሰራዊት ነው።

ቤትሌፍራ “ ‘የትቢያ ቤት’ የሚል የከተማ ስም ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ ልትሰጠው ያስፈልግህ ይሆናል።

በትቢያ ላይ እንከባለላለሁ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች የሆኑ ሰዎች ሀዘናቸውን መሪር በሆነ መንገድ ይገልጻሉ። አ.ት፡ “መሬት ላይ እንከባለላለሁ” ወይም “በጭቃ ላይ እንከባለላለሁ”።

እዚህ ጋ የመንደሮቹ የስማቸው ትርጉም ለሚክያስ አስፈላጊዎች ናቸው። በግርጌ ማስታወሻ ላይ የቦታዎቹን የስማቸውን ትርጉም ማካተት ያስፈልግህ ይሆናል።