am_tn/mic/01/06.md

1.9 KiB

X

አደርጋለሁ እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው

ሰማርያ … ድንጋዮቿ … መሠረቶቿ … የተቀረጹ ምስሎቿ … የተቀበለቻቸው ስጦታዎች … ጣዖታቷ … ስጦታዎቿን ሰበሰበች … ይሆናሉ እግዚአብሔር ከተማይቱን በሴት በመመሰል ስለ ሰማርያ ይናገራል። አ.ት፡ “ሰማርያ… ድንጋዮቿ … በከተማው ያሉ ቤቶች መሠረታቸው … በከተማው የተቀረጹት ምስሎች … ሰዎች በከተማው ውስጥ ላለው መቅደስ የሰጡት ስጦታ … በከተማው ያሉ ጣዖታት … የከተማው ሕዝብ በልጽጓል … ስጦታዎቹ … ይሆናሉ”።

ድንጋዮቿን እንዳለሁ እዚህ ጋ “እርሷ” የሚያመለክተው የሰማርያን ከተማ ነው።

የተቀረጹት ምስሎቿ ሁሉ ይደቅቃሉ ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የተቀረጹ ምስሎቿን ሁሉ አደቃለሁ”።

ስጦታዎቿ ሁሉ … በእሳት ይቃጠላሉ ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የተቀበለችውን ስጦታ በሙሉ በእሳት አቃጥለዋለሁ”

የተቀበለችው “ሰዎች የሰጧትን”

ስጦታዎቿን የዝሙት አዳሪነቷ ዋጋ አድርጋ ስለሰበሰበች አሁንም የዝሙት አዳሪነቷ ዋጋ ይሆናሉ ሰዎች የዝሙት አዳሪን እንደሚከራዩ እግዚአብሔር ለጣዖታት ስጦታዎችን ስለሚሰጡ ሰዎች ይናገራል። አሦራውያን ሰማርያን በሚያጠፉበት ጊዜ የሰማርያ ሰዎች ለጣዖቶቻቸው የሰጧቸውን ስጦታዎች ወስደው ለገዛ ራሳቸው ጣዖታት በስጦታነት ያበረክቷቸዋል።