am_tn/mic/01/05.md

1.8 KiB

X

በእስራኤል ቤት ኃጢአት ምክንያት “ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ የሚኖሩትን ቤተ ሰቦች፣ በዚህ ስፍራ ደግሞ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ በእኔ ላይ ኃጢአትን ስላደረጉ”። ይህ ሁሉ “ጌታ ይመጣና ይፈርዳል”

የያዕቆብ በደል ምንድነው? “ያዕቆብ” የሚለው ስም በሰሜናዊ እስራኤል የሚኖሩ ዘሮቹን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።

ሰማርያ አይደለችምን? እዚህ ጋ “ሰማርያ” በዚያ የሚከናወነውን ክፉ ተግባር ገላጭ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ሚክያስ ሕዝቡ እውነት ምን እንደሆነ እንዲያውቁ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ያቀርባል። አ.ት፡ “ሰማርያ መሆኗን ታውቃላችሁ”።

የይሁዳ ከፍ ያለ ቦታ ምንድነው? እዚህ ጋ “ከፍ ያለ ቦታ” ለመላው የጣዖት አምልኮ ልማድ ምሳሌ ነው። “ይሁዳ” በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች ምሳሌአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የይሁዳ ሕዝብ ጣዖትን ለማምለክ የሚሄዱት የት ነው?”

ኢየሩሳሌም አይደለችምን? በዚያ የሚከናወነውን ክፉ ተግባር ገላጭ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ሚክያስ ሕዝቡ እውነት ምን እንደሆነ እንዲያውቁ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ያቀርባል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ኢየሩሳሌም እንደሆነች ታውቃላችሁ”።