am_tn/mat/11/09.md

2.0 KiB

ማቴዎስ 11፡9-10

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 10 ላይ ኢየሱስ ከነቢይ ሚልክያስ መጽሐፍ በመጥቀስ የመጥመቁ ዮሐንስ ሕይወት እና አገልግሎት በተነገረው ትንቢት መሠረት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ነገር ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ - ነብይ ይህ ስለመጥመቁ ዮሐንስ የተጠየቁ ተከታታይ ጥያቄዎች ቀጣዩ ክፍል ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]] ተመልከት) ነገር ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ - ነብይ? አዎን እላችኋለሁ “እናንተ” የሚለው በብዙ ቁጥር የተገለጸው ተውላጠ ስም በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጥ ሕዝቡን የሚያመለክት ነው፡፡ ከነቢይም የሚበልጥ “ተራ ነቢይ ያለሆነ” ወይም “ከተራ ነቢይ በጣም የሚበልጥ” ይህ እርሱ ነው “ይህ” መጥመቁ ዮሐንስ የሚያመለክት ነው፡፡ ስለ እርሱ የተጻፈው እርሱ ነው “እርሱ” የሚው ቃል “በቀጣዩ ሀረግ ውስጥ “መልዕክተኛዬ” የተባለው የሚያመለክት ነው፡፡ መልዕክተኛዬን እልካለሁ “እኔ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው እግዚአብሔር ነው፡፡ የዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢት ጸሐፊ እግዚአብሔር የተናገረውን በቀጥታ ጽፏል፡፡ በፊትህ “ከፊትህ” ወይም “ከአንተ በፊት ይሄድ ዘንድ፡፡” “አንተ” የሚለው ተውላጠ ስም የነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ምክንያቱም በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ መስሑ የተነገረ ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት)