am_tn/mat/11/01.md

2.2 KiB

ማቴዎስ 11፡1-3

አጠቃላይ መረጃ ይህ በታሪከው ውስጥ ጸሐፊው ኢየሱስ ለመጥመቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ጥያቄ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሰጠ የሚተርከው ታሪክ ጅማሬ ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/writing-newevent]] ተመልከት) ከዚያ አለፈ ይህ ሀረግ የአዲስ ታሪክ ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የአንድ ታሪክ ጅማሬን ማሳያ መንገድ በቋንቋችሁ ውስጥ ካለ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ “ከዚያ” ወየም “ከዚያ በኋላ” በሚሉ ቃላት ሊተረጎም ይችላል፡፡ ማዘዙን ይህ ቃል “ማስተማር” ወይም “ትዕዛዝ መስጠት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ዐሥራ ሁለቱ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ይህ በኢየሱስን የተመረጡን ዐሥራ ሁለቱን ያመለክታል፡፡ አሁን “በዚያን ጊዜ”፡፡ ይህንን ሳትተረጉሙት ማለፍ ትችላላችሁ፡፡ ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ በሰማ ጊዜ አማራጭ ትርጓሜዎች፡ “በእርስ ቤት ያለው ዮሐንስ በሰማ ጊዜ” ወይም “ሌሎች ሰዎች በእርስ ላይ ላለው ለዮሐንስ በነገሩት ጊዜ” በደቀ መዛሙርቱ በኩል መልዕክትን ላከ መጥመቁ ዮሐንስ በራሱ ደቀ መዛሙርት በኩል ወደ ኢየሱስ መልዕክትን ላከ እንዲህም አለው “እርሱን” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ኢየሱስ ነው፡፡ የሚትመጣው አንተ ነህን “የሚትመጣው” ወይም “ትመጣለህ ተብለህ የሚትጠበቀው” ተብሎ ይተርጎም ይህ የሚያመለክተው መስሑን ወይም ክርስቶስን ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-euphemism]] ተመልከት) ሌላ እንፈለግ “ሌላ እንጠብቅ”፡፡ “እኛ” የሚለው ተውላጠ ስም ሁሉንም አይሁዳዊንን የሚያመለክታል እንጂ የዮሐንስን ደቀ መዛሙርት ብቻ አይደለም፡፡