am_tn/mat/10/16.md

2.9 KiB

ማቴዎስ 10፡16-18

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ሥፍራ ላይ ለመስበክ በሚሄዱበት ወቅት ስለሚያጋጥማቸው ስደት ይነግራቸው ጀምሯል፡፡ ተመልከቱ “ተመልከቱ” የሚለው ቃል በዚህ ሥፍራ ላይ ያለው ጠቀሜታ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ሀሳብ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ተመልከቱ” ወይም “አዲምጡ” ወይም “ ከዚህ በመቀጠል ለሚናረው ነገር ትኩረት ስጡ”፡፡ እልካችኋለሁ ለተወሰነ ዓላማ ኦየሱስ ልኳቸዋል፡፡ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ እንስሳት በመመሰል ሊያጠቋቸው በሚችሉ የዱር እንስሳት መካከል እንደሚልካቸው ይናገራል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-simile]] ተመልከት) እንደ በጎች በጎች ራሳቸውን መከላከል አይችሉም፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-simile]] ተመልከት) በተኩላዎች መካከል ኤቲ፡ “እንደ ተኩላ አደገኛ በሆኑ ሰዎች መካከል” ወይም “አደገኛ እንስሳት ከሚያደርጓቸው ነገሮች ጋር የሚመሳሰል ተግባር በሚያደርጉ ሰዎች መካከል” ወይም “ሊያጠቋችሁ በሚችሉ ሰዎች መካከል” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) እንደ እባብ ብልጦች እና እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ ንጽጽሩን አለመግለጡ የተሻለ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በመረዳት እና በጥንቃቄ እንዲሁም በንጹሕ ልብ እና ሥነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ ነገሮችን ፈጽሙ” ([[rc:///ta/man/translate/figs-simile]] ተመልከቱ) ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል ኤቲ፡ “ምክንያቱም ወደ ፍርድ ቤታቸው አሳልፈው ይሰጧኋል” ሸንጎዎች እነዚህ የማህረሰቡን ሰላም የሚጠብቁ የአከባቢው የሃይማኖት መሪዎችን ወይም ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ ኤቲ፡ “ፍርድ ቤቶች” ይገርፏችኋል ኤቲ፡ “በመግረፊያ ይገርፏቸኋል” አሳልፈው ይሰጧኋል “ይወስዷችኋል” ወይም “ይጎትቷችኋል” (rc://*/ta/man/translate/figs-activepassive ተመልከት) ስለ እኔ ኤቲ፡ “የእኔ ስለሆናችሁ” (UDB) ወይም “እኔን በመከተላችሁ ምክንያት” ለእነርሱና ለአሕዛብም “ለእነርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው “ገዥዎች እና ነገሥታት” ነው ወይም አይሁዳዊያን ከሳሾችን ነው (10፡17)