am_tn/mat/08/16.md

2.5 KiB

ማቴዎስ 8፡16-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር› በዚህ ሥፍራ የታሪኩ ፍሰት በዚያው ቀን ምሽት ላይ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ወደ ፈወሰበት እና ሴጣንን ከብዙ ሰዎች ወደአወጣበት ታርክ ይዞራል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 17 ላይ ጸሐፊው የኢየሱስ የፈውስ አገልግሎቱን በነብያት የተነገው ትንቢት ፍጻሜ መሆኑን ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ በመጥቀስ ጽፏል፡፡ በመሸም ጊዜ ይህ ከሰንበት በኋላ መሆኑን ያሳያል ምክንያቱም አይሁዳዊየን በሰንበት ቀን ሥራ አይሠሩም ወይም መንገድ አይሄዱም፡፡ እስኪመሽ ድረስ ጠብቀው ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፡፡ የተሳሳተ ትርጉምን ከማስወገድ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ሰንበት የሚለው ቃል መጥቀሱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-explicit]] ተመልከት) በዳብሎ የተያዙ ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ብዙ በዳብሎስ የተያዙ” (UDB) ወይም “በዳብሎስ ቁጥር ሥር የሆኑ ብዙ ሰዎች” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) በቃሉ መናፍስቱን አስወጣ በዚህ ሥፍራ “ቃል” የሚለው ቃል ትርጉሙ ትዕዛዝ ነው፡፡ ኤቲ፡ “መንፈሱ እንዲወጣ አዘዘ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) በነብይ ኢሳያስ የተነገረው ትንቢትን ይፈጽም ነበር ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ነብዩ ኢሳያስ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው የትንቢት ቃልን ኢየሱስ ፈጸመው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]]) ተመልከት) ድካማችን ተቀበለ ደዊያችንንም ተሸከመ ማቴዎስ ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠቅሷል፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሀረጋት በመሠረታዊ መልዕክታቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለቱም አጽኖት የሚሰጡት እርሱ ሁሉንም በሽታችንን ፈውሷል፡፡ ኤቲ፡ “የታመሙትን ፈውሷል እንዲሁም ደና አድርጓቸዋል፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-parallelism ተመልከት)