am_tn/mat/08/04.md

1.4 KiB

ማቴዎስ 8፡4-4

ለእርሱ ይህ ኢየሱስ የፈወሰውን ሰው ያመለክታል፡፡ ለማንም አትናገር “ለማንም ምንም አትናገር” ወይም “እኔ እንደፈወስኩህ ለማንም አትናገር” ለካህናት ራስህን አሳይ የአይሁዳዊያን ሕግ የተፈወሰ ሰው ቆዳውን ለካህናት ማሳየት እንዳለበት ይጠይቃል፡፡ እነርሱም ቆዳውን ከተመለከቱ በኋላ ከሕዝቡ ጋር እንዲቀላቀል ይፈቅዱለታል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-explicit]] ተመልከት) ለእርሱ ምስክር ይሆንህ ዘንድ በሙሴ ትዕዛዝ መሠረት መስዋዕትን አቅርብ በሙሴ ሕግ መሠረት ከለምጽ የተፈወሰ ሰው የምስጋና መስዋዕትን ለከካህናት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ካህናቱ ስጦታውን ከተቀበሉ ሕዝቡ ይህ ሰው መፈወሱን ያውቃሉ፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-explicit]] ተመልከት) ለእነርሱ ይህ የሚያመለክተው 1) ካህናትን ወይም 2) ሌሎች ሰዎችን ወይም 3) ኢየሱስን የሚተቹ ሰዎችን ሊሆን ይችላል፡፡ ከተቻለ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል ዬትኛውንም የሚያመለክትን ስም ተጠቀሙ፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-pronouns ተመልከት)