am_tn/mat/07/07.md

3.1 KiB

ማቴዎስ 7፡7-10

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ተገልጸዋል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት)፡፡ ጠይቁ . . . ፈልጉ . . . አንኳኩ ይህ ወደ እግዚአብሔር መጸለይን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ግሥ እግዚአብሔር ምላሽ እስኪሰጠን ድረስ እንዲንጸለይ የሚያደርግ ነው፡፡ በቋንቋችሁ አንድን ነገር መልሳችሁ መልሳችሁ ማድረግ እንዳለባችሁ የሚገልጽ ቃል ካለ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) ጠይቁ ይህ ከእግዚአብሔር የሆነ ነገርን ጠይቁ ማለት ነው፡፡ (UDB) ይሰጣችኋል ይህ እንዲህ ባለ መልኩ በቀጥታ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “የሚያስፈልጋችሁን ነገር እግዚአብሔር ይሰጣችኋል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) ፈልጉ “ስለምትፈልጉትን ነገር የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ” አንኳኩ በር ማንኳኳት በቤት ውስጥ ያለ ሰው በሩን እንዲከፍትላችሁ በትህትና መጠየቅ ነው፡፡ በእናንት ባሕል ውስጥ በር ማንኳኳት ትህትና ካልሆነ ሰዎች በእናንተ ባሕል ውስጥ በር እነንዲከፈትላቸው በትህትና የሚጠይቁ በምን ዓይነት መንገድ ነው፣ ይህንንም ቃል ተጠቀሙ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር በሩን እንዲከፍትላችሁ እንደሚትልጉ ንገሩት፡፡” ወይም ከእናንተ መካከል ማን ነው . . . ድንጋይ? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ ኤቲ፡ “ከእናንተ መካከል ማንም የለም . . . ድንጋይ፡፡” ( [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]] ተመልከት) ቁራጭ ዳቦ ይህ በአጠቃላይ ምግብን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “የሆነ ምግብ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-synecdoche]] ተመልከት) ድንጋይ. . . ዓሳ . . . እባብ እነዚህ ስሞች በቁማቸው መተርጎም አለባቸው፡፡ ወይም ኣሳ ጠይቋችሁ እባብ የምትሰጡት? ኢየሱስ ለማስተማር ሌላ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ሥፍራም ኢየሱስ ስለ ሰውዬው እና ልጁ እየተናገረ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ከእናንተ መካከል ልጁ ዓሳ ጠይቆት እባብ የሚሰጠው ማንንም የለም፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]] እና rc://*/ta/man/translate/figs-ellipsis ተመልከት)