am_tn/mat/06/22.md

2.9 KiB

ማቴዎስ 6፡22-24

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “አንተ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ በዋለባቸው ሥፍራዎች ውስጥ በነጠላ ቁጥር የተጠቀሰ ሲሆን አንተ ግን በብዙ ቁጥር ለመተርጎም ታስብ ይሆናል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት) ዐይን የሰውነት ብርሃን ነች . . . ጨለማው ምን ያኽል ታላቅ ይሆን ይህ ማየት የሚችል ጤናማ ዐይንን አንድን ሰው ዐይነ ሥውር ከሚያደረግ በሽታ ጋር ያነነጻጽራል፡፡ ይህ ምሳሌ የሚያመለክተው መንፈሳዊ ጤንነትን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አይሁዳዊያን “መጥፎ ዐይንን” ከስስት ጋር ያይዙታል፡፡ ትርጉሙም አንድ ሰው ሁለተናውን ለእግዚአብሔር ከሰጠ እንዲሁም ሁሉንም ነገር ከእግዚአብሔር አንጻር መመልከት ከቻለ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ስስታም ከሆነ ክፋትን ያደርጋል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) ዐይን የሰውነት ብርሃን ነው የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉም ልክ መብራት በጨለማ ውስጥ ሰው አጥርቶ እንዲያይ እንደሚያደርግ ሁሉ ዐይንም አንድ ሰው በደንብ ማየት እንዲችል ያደርገዋ፡፡ ኤቲ፡ “እንደ መብራት ዐይን ነገሮችን በግልጽ ማየት እንድትችል ያደርጋል፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) ዐይን ይህንን በብዙ ቁጥር ልትተረጉመው ትችላለህ፤ “ዐይኖች”፡፡ ዐይንህ መጥፎ ቢሆን ይህ ምትሃትን አያመለክትም፡፡ አይሁዶች ብዙ ጊዜ ስስታምነትን በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ይገልጹታል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) አንዱን ይወዳል ሌላኛውን ይጠላል ወይም ለአንዱ ይገዛል ሌላኛውን ደግሞ ይንቃል ሁለቱም በመሠረታዊ ሀሳባቸው አንድ ናቸው፡፡ አጽኖት የሚሰጡት አንድ ሰው እግዚአብሔር መውደድ እና መገዛት እንዲሁም ገንዘብንም መውደድና ለእርሱ መገዛት በአንድ ጊዜ አይችልመም፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-parallelism ተመልከት) ለሀብት እና ለእግዚአብሔር መገዛት አትችሉም፡፡ “በአንድ ጊዜ እግዚአብሔርን እና ገንዘብን መውደድ አትችሉም፡፡”