am_tn/mat/05/40.md

2.2 KiB

ማቴዎስ 5፡40-42

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ፍቀድ”፣ “ሂድ”፣ “ስጥ” እና “አትመለስ” በሚሉ ቃላት ውስጥ ያለው “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት) ኮትህ . . . መጎናጸፊያ “ኮት” በሰዉነት ላይ እንደ ቲሸረት የሚጠለቅ ነው፡፡ “መጎናጸፊያ” ከእነዚህ ይልቅ ውድ የሆነ “ከኮት” ላይ ለሙቀት የሚደረብ እንዲሁም በሽት ለሙቀት የሚለበስ ነገር ነው፡፡ ይወስድ ዘንድ ፍቀድለት “ለዚያ ሰው ስጠው” ማንምን ሰው “እንዲሁም ይህ ሰው”፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ በተዘዋዋር መንገድ የተጠቀሰው የሮማዊያን ወታደር ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-explicit]] ተመልከት) አንድ ምዕራፍ አንድ የሮም ወታደር በዚያ ዘመን አንድን ሰው አንድ ዕቃ ተሸክሞ እንዲሄድ በሕግ ማስገደድ የሚችለው አንድ ሺህ እርምጃዎች ያኽል ነው፡፡ “ማይል” የሚለው ቃል የሚያምታታ ከሆነ “አንድ ኪሎ ሜትር” ወይም “ረጅም ርቀት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ከእርሱ ጋር አብረኸው እንዲትሄድ ያስገደደ ሰውን ያመለክታል፡፡ ከእርሱ ጋር እጥፍ መንገድ ሂደት “አስገድዶህ እንዲትሄድ ያደረግህን ምዕራፍ ያኸል ሂደት ከዚያም ሌላ አንድ ማዕራፍ ጨምርለት፡፡” “ማይል” የሚለው ቃል የሚያምታታ ከሆነ “ሁለት ኪሎ ሜትር” ወይም “እጥፍ ርቀት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አትከልክል “እንዲሁም ሊበደርህ የሚፈልግ ሰውን አትከልክል፡፡” ይህ በአውንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይገባል፡፡ ኤቲ፡ “አበድር”፡፡