am_tn/mat/04/23.md

2.3 KiB

ማቴዎስ 4፡23-25

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ይህ ኢየሱስ በገሊላ የጀመረው አገክግሎት ታሪክ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ምን እንዳደረገ እና ሰዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆነ ጠቅለል አድርጎ ያሳየናል፡፡ (End of Story ተመልከት)

በምኩራቦቻቸው እያስተማረ “በገሊላ ውስጥ በሚገኙ ምኩራቦች ውስጥ እያስተማረ” ወይም “በእነዚህ ሰዎች ምኩራብ ውስጥ እያስተማረ፡፡”

የመንግስቱን ወንጌል እየሰበከ በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚብሔር ንጉሥ ሆኖ መንገሡን ነው፡፡ ኤቲ፡ “ወንጌልን ማለትም እግዚአብሔር እንዴት ራሱን ንጉሥ አድርጎ እንደገለጠ እየሰበከ” (UDB) (rc://*/ta/man/translate/figs-metonymy ተመልከት)

ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እና ደዌዎች “ማንኛውንም በሽታ እና ደዌ፡፡” “በሽታ” እና “ደዌ” የሚሉት ቃላት በጣም የተቀራረቡ ናቸው ነገር ግን ከተቻለ በሁለት የተያዩ ቃላት አማካኝነት ቢተረጎሙ መልካም ነው፡፡ “በሽታ” አንድ ሰው አንዲታመም የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ “ደዌ” አካላዊ ድክመት ወይም በሽተኛ በመሆን በአካል ላይ የሚሆን ህመም ነው፡፡

በዳቢሎስ የተያዙ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በዳቢሎስ የተያዘ” ወይም “ዳቢሎስ የተቆጣጠራቸው፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-activepassive ተመልከት) የሚጥል በሽታ “የሚጥል በሽታ ያለባቸው” ወይም “ካለባቸው በሽታ የተነሳ የሚወድቁትን”

ሽባዎችን “መራመድ የማይችሉትን” ከዐሥሩም ከተሞች ይህ “ዐሥር ከተማዎች” ስም ነው፡፡ ." (UDB) ይህ ከገሊላ ባሕር በደቡብ ምስራቅ በኩሉ የሚገኘውን አከባቢ መጠሪያ ስም ነው፡፡ (rc://*/ta/man/translate/translate-names ተመልከት)