am_tn/mat/04/05.md

2.3 KiB

ማቴዎስ 4፡5-6

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 6 ላይ ሴጣን ከመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ውስጥ ኢየሱስን ለመፈተን ሲል የሆነ ሀሳብ ስወስድ እናያለን፡፡

አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደታች ወርውር የዚህ ሀረግ አማራጭ ትርጉሞች 1) 1) ይህ ፈተና ኢየሱስ ለራሱ ጥቅም ተዓምራትን ይሠራ ዘንድ የቀረበ ፈተና ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆንህ ራስህን ወደታች መወርወር ትችላለህ፡፡” ወይም 2) ይህ የሚያመለክተው በኢየሱስ ላይ የቀረበውን ክስ ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆንህ ራስህን ወደታች በመወርወር አረጋግጥ፡፡” (UDB) ሴጣን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እንደሚያውቅ ማሰቡ ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከሎ ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ ስም ነው፡፡ (rc://*/ta/man/translate/guidelines-sonofgodprinciples ተመልከት)

ራስህን ወደታች ወርውር “ወደታች ራስህን ወርውረህ ውደቅ” ወይም “ወደታች ዝለል”

እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና ይህ በዚህ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መዝሙረኛው በመመጽሐፉ ውስጥ አንዲህ ብሎ ጽፏልና” ወይም “በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ተብሏልና፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-activepassive ተመልከት)

ይጠብቁህ ዘንድ መልአክቱን ስለአንተ ያዛልና “አንተን እንዲጠብቁህ እግዚአብሔር መልአክቱን ስለአንተ ያዛል፡፡” ይህ እንዲህ ተብሎ በትምህረተ ጥቅስ ውስጥ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ለመልአክቱ እንዲህ ይላቸዋል፣ “ጠብቁት፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-quotations ተመልከት)

ያነሱሃል “መልአክቱ ይይዙሃል”