am_tn/mat/04/01.md

3.4 KiB

ማቴዎስ 4፡1-4

አጠቃላይ መረጃ በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው ኢየሱስ በምድረ በዳ 40 ቀናትን ያሳለፈበትን፣ በሴጣን የተፈተነበትን የታሪኩን አዲስ ክፍል ይጀምራል፡፡ በቁጥር 4 ላይ ኢየሱስ ከዘዳግም መጽሐፍ በተወሰዱ ጥቅሶች አማካኝነት ሴጣንን ስገስጸው እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስ በመንፈስ ተመርቶ

ይህ በቀጥታ በዚህ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መንፈስ ኢየሱስን መራው፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) በዳብሎስ ይፈተን ዘንድ ይህ በቀጥታ በዚህ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ዳብሎስ እርሱን መፈተን ይችል ዘንድ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) ዳቢሎስ . . . ፈታኙ እነዚህ ሁለት ቃላት የሚያመለክቱት አንድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱን ለመተርጎም አንድ ቃል መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ጾመ . . . ተራበ ይህ ስለኢየሱስ የተባለ ነው፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እዘዝ የዚህ ሀረግ አማራጭ ትርጓሜዎች 1) ይህ ፈተና ኢየሱስ ለራሱ ጥቅም ተዓምራትን ይሠራ ዘንድ የቀረበ ፈተና ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስለዚህ ማዘዝ ትችላለህ፡፡” 2) ይህ የሚያመለክተው በኢየሱስ ላይ የቀረበውን ክስ ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህ ትዕዛዝ በመስጠት አረጋግጥ፡፡” ሴጣን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እንደሚያውቅ ማሰቡ ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከሎ ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ ስም ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/guidelines-sonofgodprinciples]] ተመልከት) ድንጋዩ ዳቦ እዲሆን እዘዝ ይህንን በቀጥጣ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ለእነዚህ ድንጋዮች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ ዳቦ ሁኑ!” ([[rc:///ta/man/translate/figs-quotations]] ተመልከት)

ዳቦ ኤቲ፡ “ምግብ” (rc://*/ta/man/translate/figs-synecdoche ተመልከት)

እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ሙሴ ከብዙ ዘመናት በፊት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-activepassive ተመልከት)

የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ አይኖርም ይህ በቀላሉ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከምግብ በላይ ሌላ በጣም አስፈላጊ ነገር አለ ማለት ነው፡፡

ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ማንኛውም ቃ እንጂ በዚህ ሥፍራ “ቃል” እና “አፍ” የሚሉ ቃላት እግዚአብሔር የተናገራቸውን ነገሮችን ያመለክታሉ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ነገሮች በማድመጥ እንጂ፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-metonymy ተመልከት)