am_tn/mat/03/07.md

2.8 KiB

ማቴዎስ 3፡7-9

አጠቃላይ መረጃ መጥመቁ ዮሐንስ ፈርሳዊያንን እና ሳዱቃዊያንን ይገስጻቸው ጀመረ፡፡ እናንተ የመርዛማ እባብ ልጆች ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ መርዛማ እባቦች አደገኛ ናቸው እንደሁም ክፋትን ይወክላሉ፡፡ ኤቲ፡ “እናንተ መርዛማ እባቦች!” ወይም “ልክ እንደ መርዝማ እባቦች ክፉዎች ናችሁ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ ዮሐንስ ፈርሳዊያንን እና ሳዱቃዊያንን ለማስጠንቀቅ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዳይቀጣቸው ዮሐንስ ያጠምቃቸው ዘንድ ይጠይቁት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኃጢአት ማድረጋቸውን ማቆም አይፈልጉም ነበር፡፡ ኤቲ፡ “በዚህ ዓይነት መንገድ ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ አይቻልም፡፡” ወይም “እኔ ስላጠመኳችሁ ከእግዚአብሔር ፍርድ የሚታመልጡ አይመስላችሁ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]] ተመልከት) ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ “ቁጣ” የሚለው ቃል በዚህ ሥፍራ ጥቅም ላይ የዋለው የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማመለከት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ይህ ከእግዚአብሔር ቅጣት ቀድሞ የሚመጣ ስለሆነ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ” ወይም “ከእግዚአብሔር ቅጣት ለማምለጥ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) የንሰሓን ፍሬ አፍሩ “አፍሩ” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን የሰውዬውን ተግበባራት ያሳያል፡፡ ኤቲ፡ “ተግባራችሁ በእውነት ንሰሓ እንደገባችሁ ያሳይ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) አባታችን አብረሃም አለልን “አብረሃም አባታችን ነው” ወይም “እኛ የአብረሃም ዘሮች ነን፡፡” የአይሁድ መሪዎች የአብረሃም ዘሮች በመሆናቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደማይቀጣቸው ያስቡ ነበር፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-explicit ተመልከት) እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ ይህ ዮሐንስ ቀጥሎ ስለሚናር ነገር አጽኖት እንድሰጠ ያሳያል፡፡ ከእነዚህ ድንጋዮች እግዚአብሔር ልጆችን ማስነሳት ይችላል “ከእነዚህ ድንጋዮች ሳይቅር እግዚአብሔር ለአብረሃም ለልጆችን አበጅቶ ለአብረሃም መስጠጥ ይችላል፡፡”