am_tn/mat/02/01.md

2.7 KiB

ማቴዎስ 2፡1-3

አጠቃላይ መረጃ የታሪኩ አዲስ ክፍል የሚጀምረው በዚህ ሥፍራ ላይ ነው፡፡ ከዚያም እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ይሄዳል፡፡ ጸሐፊው ሄሮዶስ አዲሱን የአይሁድ ንጉሥ ለመግደል ስላደረገው ሙከራ ይነግረናል፡፡ ቤተልሔም ይሁዳ “በይሁዳ ግዛት ውስጥ የሚትገኝ የቤተልሔም ከተማ” ሄሮዶስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን “በዚያ ሄሮዶስ ንጉሥ ሆኖ ሳለ” ሄሮዶስ ሄሮዶስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ታላቁን ሄሮዶስን ነው፡፡ የተማሩ ሰዎች “ክዋክብትን ያጠኑ ሰዎች” (UDB) ከምስራቅ የመጡ “ከይሁዳ በስተምስራቅ በኩል ከሚገኝ ሀገር የመጡ” የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ዬት አለ? ሰዎቹ ከክዋክብት ጥናታቸው የአይሁድ ንጉሥ ለመሆን የተወለደ ልጅ እንዳለ አውቀዋል፡፡ በዬት ሥፍራ እንዳለ ለማወቅ ፈልገዋል፡፡ ኤቲ፡ “የአይሁድ ንጉሥ ለመሆን አንድ ልጅ ተወልዷል፡፡ ዬት ነው ያለው?” የእርሱ ኮከብ ኮከቧ ትክክለኛ ባለቤት ልጁ ነው እያሉ አይደለም፡፡ ኤቲ፡ “ስለ እርሱ የሚትናገረው ኮከብ” ወይም “ከእርሱ መወለድ ጋር የተያያዘችው ኮከብ” በምስራቅ “በምስራቅ በወጣች ጊዜ” ወይም “በሀገራችን ሳለን” ማምለክ አማራጭ ትርጉሞች 1) ልጁ መለኮት እንደሆነ ተገንዝበወ ለማምለክ ፈልገዋል ወይምመ 2) እንደ አንድ ንጉሥ ልያከብሩት ፈልገዋል፡፡ ቋንቀዋችሁ ሁለቱንም ትርጉሞች መያዝ የሚችል ቃል ካለው በዚህ ሥፍራ ላይ ይህንን ቃል መጠቀምንን ከግንዛቤ ውስጥ አስገቡ፡፡ ተጨነቀ “ፈራ”፡፡ ይህ ልጅ ንግሥናዬን ይቀማኛል ብሎ በመፍራት ተጨነቀ፡፡ ኢየሩሳሌም በሙሉ በዚህ ሥፍራ ላይ “ኢየሩሳሌም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎችን ነው፡፡ እንዲሁም “ሁሉም” ማለት “ብዙ” ማለት ነው፡፡ ማቴዎስ በዚህ ሥፍራ ላይ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ መጨነቃቸውን ለማመልከት ግነት ተጠቅሟል፡፡ ኤቲ፡ “በኢየሩሳሌም ያሉ ብዙ ሰዎች፡፡” (UDB) ( [[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] and [[rc:///ta/man/translate/figs-hyperbole]] ተመልከት)