am_tn/mat/01/22.md

1.8 KiB

ማቴዎስ 1፡22-23

አጠቃላይ መረጃ ጸሐፊው የኢየሱስ አወላለድ በቅዱሳት መጽሐፍት አስቀድሞ በተነገረው መሠረት መሆኑን ለማሳየት ከነብይ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሶዋል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/writing-background]] ተመልከት) ይህ ሁሉ ሆነ መልአኩ መናገር አቁሟል፡፡ አሁን ማቴዎስ መልአኩ የተናገረው ነገር ምን ያኽል አስፈላጊ እንደሆነ እያብራራ ነው፡፡ ጌታ በመላዕክቱ አማካኝነት የተናገረው ነገር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “ጌታ ለነብይ ኢሳያስ ከብዙ ዘመናት በፊት የተናገረው እንዲጽፍ የነገረው ነገር፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) እነሆ . . . አማኑኤል በዚህ ሥፍራ ላይ ማቴዎስ ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡ እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡ ኤቲ፡ “ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”:: አማኑኤል ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (rc://*/ta/man/translate/translate-names ተመልከት) “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው ይህ በኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ የለም፡፡ ማቴዎስ የስሙን ትርጉም እያብራራ ነው፡፡ ይህን ለብቻው በአንድ ዐረፍተ ነገር መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ ኤቲ፡ “የዚህ ስም ትርጉም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው፡፡