am_tn/mal/04/04.md

1.7 KiB

በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ትምህርት ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ

“ትምህርት” የተባለው የተማሩትን ለማለት ነው። ስለዚህ “ አገልጋዬን ሙሴን ያስተማርኩትን” ይባል።

አስታውሱ

በዚህ ስፍራ “አስታውሱ” የተባለው “ ስለዚህ ነገር አስቡ” እንዲሁም “ታዘዙዝ” ለማለት ነው።

ሆሬብ

ይህ የሲና ሌላው ስም ነው።

እስራኤል ሁሉ

በዚህ ስፍራ “እስራኤል ሁሉ” የሚለው በእስራኤል አገር የሚኖሩትን ሕዝብ ለማለት ነው።

ሕጉን/ደንብ

ይህ ሕግ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሁሉ የሰጠው ነው።

ትዕዛዞች

እነዚህ ሕጋዊ ዉሳኔዎች በየእለቱ በህይወታቸው በአጠቃላይ ሕጉ እንዴት ስራላይ ሊዉል እንደሚችል ግልጽ የሚያደርጉ ናቸው።

ታላቁና አስፈሪው የእግዚአብሔር ቀን መምጣት

የዚህ ቀን መምጣት የተገለጸው እየመጣ ነው በማለት ነው።ስለዚህ “ታላቁና አስፈሪው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት” ይባል።

ታላቁና አስፈሪው የእግዚአብሔር ቀን

ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው እግዚአብሔር የመከራ ቀን የሚያመጣበትን ጊዜ ነው።

እርሱ የወላጆችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ ወላጆች ይመልሳል

በዚህ ስፍራ ይመልሳል/ ይለዉጣል የተባለው ልባቸውን ይመልሳል ለማለት ነው።