am_tn/mal/02/13.md

1.1 KiB

መሠዊያውን በእንባ ትከድናላችሁ።

ይህ አባባል በፌዝ መልክ በማጋነን የሰዎቹን እንባና ለቅሶ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ሰዎቹ ምንም ሀዘን አይሰማቸውም ለማለት ነው።

በለቅሶና በሀዘን

“ለቅሶ” እና “ሀዘን” የሚሉ ቃላት በተመሳሰለ አገላለጽ ለቅሶ የሚለዉን ሃሳብ ለማጠንከር ነው። ስልዚህ “በከፍተኛ ለቅሶ” ይባል።

እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥

እዚህ ላይ ቁርባኑን አይመለከትም የሚለው ስጦታውን በመቀበል ለሰጪው አድልዖ ማድረግን ያሳያል።

እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት

ይህም የሚያመለክተው እነዚህ በእግዚአብሔር መሰውያ ላይ የሚያለቅሱ ሰዎች መሰዋዕት ለእሱ እንዳቀረቡ ነው።

ከእጃችሁ

በዚህ ስፍራ “እጅ” የሚለው የሚያመለክተው ሰጭው ስጦታ መስጠቱን ነው።