am_tn/mal/02/10.md

4.2 KiB

ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?

ሚልክያስ የሱ ወገን የሆኑትን እስራኤላውያንን ቀደም ሲል የሚያውቁትን ነገር ለማሳሰብ ጥያቄ ይጠይቃቸዋል፤ ስለሆነም መባል ያለበት “ሁላችንም አንድ አባት ያለን፤የእኛ አምላክም ከእኛ አንድ ህዝብ እንደፈጠረ ታውቃላችሁ” ወይም “ሁላችሁም እንደምታዉቁት እግዚአብሔር የእስራኤላውያን ሁሉ አባት ነው፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር መንግስታችንን/ሕዝባችንን የመሰረተው እሱ ስለሆነ ነው”።

አንድ አምላክስ አልፈጠረምን?

ይህጥያቄ የሚገልጸው ቀጥሎ ያለዉን አረፍተነገር ነው፤ “በእርግጥ አንድ አምላክ ሁላችንንም ፈጥሮናል”።

ፈጥሮናል

ይህ አረፍተነገር የሚያሳየው እግዚአብሔር አይሁዳውያንን አንድ ህዝብ እንዲሆኑ ማድረጉ ነው።

የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?

ሚልክያስ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው የራሱ ወገን የሆኑትን እስራኤላውያንን ለመገሰጽ ፈልጎ ነው። ስለዚህ ይህ ጥያቄ ቀጥሎ ባለው መንገድ ወደ አረፍትነገር ሊቀየር ይችላል። “አሁን እንደምታደርጉት እኛ በእርግጥ ወንድሞቻችንን በክፉ በማየትና ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን ማቃለል የለብንም”።

ይሁዳ አታልሎአል

በዚህስፍራ “ይሁዳ” የሚለው ቃል አይሁዳውያን የሚኖሩበት ስፍራ ያሉትን የአይሁድ ህዝብ ሲወክል ለእግዚአብሔር አለመታመናቸውን ለመግለጽ “ይሁዳ” ብሎዋል። ስለዚህ “የአይሁድ ህዝብ ለእግዚአብሔር አልታመነም” ይባል።

በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል

ይህንን አገላለጽ ቀጥሎ ባለው መንገድ ማቅረብ ይቻላል፤ “በእስራኤልና በእየሩሳሌም ያሉ ሰዎች አስጸያፊ ነገሮችን ሰርተዋል”።

እግዚአብሔር ቅዱስ ስፍራ ይሁዳ ስላረከሰ

በዚህ ስፍራ “ይሁዳ” የእስራኤልን ህዝብ ይወክላል።ስልዚህ “የይሁዳ ህዝብ/አይሁዳውያን የተቀደሰውን የእግዚአብሔርን ስፍራ ስላረከሱ” ሊባል ይችላል።

የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና

በዚህ ስፍራ የይሁዳ ህዝብ እንደ አንድ ሰው ስም ”ይሁዳ” ተብለዋል። ስለሆነም ፤ “ይሁዳ ጣዖት አምላኪ የሆነች የሌላ አገር ህዝብ ሴት አግብቶአል” ይባል።

እንዲህ የሚያደርገውን ሰው እግዚአብሔር ከያዕቆብ ድንኳን ቆርጦ ያጥፋው

በዚህ ስፍራ አንድን ነገር ማጥፋት ማላት ከአንድ ነገር ላይ ቆርጦ መጣል ማለት ነው።ስለሆነም “እንደዚህ የሚያደርገውን ሰው እግዚአብሔር ያጥፋው” ወይም “ከእስራኤል ህዝብ መካከል እንደዚህ የሚያደርገውን ሰው እግዚአብሔር ይግደለው” ይባል።

የያዕቆብ ድንኩዋን

በዚህ ስፍራ “የያዕቆብ ድንኩዋን” የሚያመለክተው የእስራኤል ህዝብ ነው።

ያዕቆብ

በዚህ ስፍራ “ያዕቆብ” የሚያመለክተው እስራኤላውያንን ነው፥ ምክንያቱም እስራኤላውያን ሁሉ የከያዕቆብ ተወላጆች ስለሆኑ ነው።

እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን

ይህ አገላለጽ “አንድም ሳይቀር ሁሉንም” ለማለት ነው።