am_tn/mal/02/08.md

1.4 KiB

እናንተ ግን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ ብላችኋል

ቀጥተኛና ትክክለኛ የሆነውን መንገድ መከተል ለማለት ነው።

ብዙዎች እንዲሰናከሉ አድርጋችሁዋል

ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ እንደማሰናከል ይቆጠራል።

በሕግም ብዙዎች እንዲሰናከሉ አድርጋችሁዋል

“በሕግም” የሚለው አገላለጽ “መሰናከል” የሚለውን አውድ ይሰጣል። ስለዚህ “እናንተ ብዙዎች ለሕጉ እንዳይታዘዙ አድርጋችሁዋል” ይባል።

በሕዝብ ሁሉ ፊት

ይህ ሃሳብ ሕዝቡ የካህናቱን ክፉ ባህሪይ ማወቃቸውን ያመለክታል።

መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ

በዚህስፍራ “መንገድ” የሚለው “ፍላጎት” ወይም “ባህሪይ” የሚለዉን ያመለክታል።

በሕግም ለሰው ፊት አዳልታችሁዋል

“ለምትወዱአቸው ሰዎች ቀላል ምስፈርት ስታስቀምጡ፤ ለምትጠሉዋቸው ሰዎች ግን አስቸጋሪ መስፈርት ታስቀምጣላችሁ”።

አድልዖ ማሳየት

በዚህ ስፍራ አንድን ሰው ከሌላው አብልጦ መውደድን ያመለክታል፤ስለዚህ “አንዱን ከሌላው አስበልጣችሁ እንድምትወዱ እወቁ” ይባል።