am_tn/mal/02/03.md

2.1 KiB

ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ

እዚህ ላይ “ፋንድያ በፊታችሁ ላይ” የሚለው ሐረግ ማዋረድ/ ማሳፈር የሚለውን ለማመልከት ነው።

የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ

እዚህ ላይ “መሰዋዕት” የሚለው ቃል በእስራኤል በእላት ላይ ካህናት ለመሰዋእትን እንስሳት ይመለከታል። “ፋንዲያ/እበት” የሚለው ቃል እንስሳቱ ለመሰዋዕት ከመታረዳቸው የሚጥሉትን ቆሻሻ ወይንም ከታረዱ በሁዋላ ስጋቸው ሲበለት ከሰውነታቸው የሚወጣውን ለማመልከት ሊሆን ይችላል። የቤተመቅደስ ሰራተኞች እበቱን ከቤተመቅደሱ ዉጪ ወይንም ከእየሩሳሌም ዉጪ ይጥሉታል።

ከእርሱም ጋር በአንድ ላይ ይወሰዳችሁዋል

ይህ ለትርጉም የሚያስቸግር አገላለጽ ቢሆንም እንደዚህ ማለት ይቻላል “እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር( ከእበቱ ጋር) ይወስዳችሁዋል። ስለሆነም “በእበት መጣያ ላይ ይወረውሩአችሁዋል፤እግዚአብሔር በእርግጥ ከእበት መጣያ ጋር እንድትወሰዱ ያደርጋል”።

ከእርሱም ጋር በአንድ ላይ ይወሰዳችሁዋል

ለዚህ አባባል ሁለት አማራጮች አሉ፤ 1) እግዚአብሔር ታማኝ ያልሆኑትን ካህናት በሞት በመቅጣት ሬሳቸው ከእንስሳት እበት መጣያ ላይ እንዲጣሉ ያደርጋል ወይንም 2) እግዚአብሔር ታማኝ ያልሆኑትን ካህናት በአስከፊና በአሰቃቂ ሁኔታ በሞት በመቅጣት ሬሳቸዉን ከእንስሳት ፋንዲያ ጋር እንዲጣሉ ያደርጋል።

ሌዋዊ

በዚህ ስፍራ ሌዋዊ የሚለው ቃል የሌዊን ተወላጆችና ዘሮቹን ለማለት ነው። ስለዚህ “ ቃልኪዳኔ ከእናንተ ከሌዊ ዘሮች ጋር ነው” ይባል።