am_tn/mal/01/10.md

1.7 KiB

ከሆነ ብቻ

የከፍተኛ ፍላጎት መግለጫ

በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ

በዚህ ስፍራ “በመሰውያየ ላይ እሳት ማቃጠል” የሚለው የሚያመለክተው ለእግዚአብሔር መሰዋእት በመሰውያው ላይ ማቅረብን ነው።ስለሆነም “ተቀባይነት የሌለውን ስጦታ ማቃጠል ተገቢ አይደለም” ይባል።

ከእጃችሁ

እዚህ ላይ “እጃችሁ” የሚለው “እናንተ” የሚለውን ይወክላል። ስለሆንም “ከእናንተ” ይባል።

ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ

ይህ አገላለጽ “በሁሉም ስፍራ” ለማለት ነው።

ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና

እዚህ ላይ “የኔ ስም” የሚለው አባባል የእግዚአብሔርን ዝናና ክብር ለማመልከት ነው። ስለሆነም “በሌሎች ህዝቦች ላይ እከብራለሁ” ይባል።

በሁሉም ስፍራ ዕጣንና ንጹህ ስጦታ በስሜ ይቀርባል

ይህ አገላለጽ እንደሚከተለው ሊቀርብ ይችላል፡ “ከእነዚህ አገሮች ሰዎች እኔን ለማምለክ እጣንና ንጹህ ስጦታን ያቀርባሉ”።

በኔ ስም

በዚህ ስፍራ “ስም” እግዚአብሔርን ይወክላል። ስለሆነም “ለኔ” ይባል።

ፍሬው፥ መብሉም

አማራጭ ትርጉሞች 1) “በመሰውያ ላይ የተሰዋ የእንስሳት ስጋ ሆኖ ከብልቱ ካህናት የሚበሉት” ወይም 2) በመሰውያ ላይ የተሰዋ ስጋ”