am_tn/luk/23/39.md

1.7 KiB

ሰደቡት

‹‹ኢየሱስን ሰደቡት››

አንተ ክርስቶስ አይደለህንም? ራስህን አድን

ወንጀለኛው ጥያቄውን ያቀረበው በኢየሱስ ለማፌዝ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክርስቶስ ነኝ ብለሃል፤ ራስህን አድን›› ወይም፣ ‹‹አንተ በእርግጥ ክርስቶ ከሆንህ ራስህን ማዳን ነበረብህ››

ራስህንና እኛን አድን

ወንጀለኛው ኢየሱስ ከመስቀል እንደሚያድናቸው በእርግጥ አያስብም፡፡

ሌላው ገሠጸው

‹‹ሌላው ወንጀለኛ ገሠጸው››

ተመሳሳይ ፍርድ እየተቀበልህ ሳለህ ከቶ እግዚአብሔንር አትፈራምን?

ወንጀለኛው ጥያቄውን ያቀረበው ሌላውን ወንጀለኛ ለመገሠጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔርን መፍራት አለብህ ምክንያቱም እርሱን በቀጡበት መንገድ አንተንም እየቀጡህ ነው፡፡ ወይም፣ ‹‹እንደ እርሱ ሁሉ አንተም መስቀል ላይ ተሰቅለህ ሳለ እርሱ ላይ በማፌዝህ እግዚአብሔንር አትፈራም ማለት ነው››

እኛ ላደረግነው… ቅጣት… ይገባናል

‹‹እኛ›› የሚያመለክተው ሁለቱን ወንጀለኞች እንጂ፣ ኢየሱስን ወይም ሌሎችን ሰዎች አይደለም፡፡

እኛ እዚህ መሆናችን ተገቢ ነው

‹‹በእውነት እኛ ይህ ቅጣት ይገባናል››

ይህ ሰው

ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው