am_tn/luk/23/36.md

1.1 KiB

እርሱ

ኢየሱስ

ወደ እርሱ ቀርቦ

‹‹ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ››

የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ሰጠው

‹‹ኢየሱስ እንዲጠጣ የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ቀረበለት›› ኮምጣጣ ወይን ጠጅ ማንኛውም ሰው የሚጠጣው ተራ መጠጥ ነው፡፡ ንጉሥ ነኝ ይል ለነበረው ርካሽ መጠጥ በመስጠት ወታደሮቹ በኢየሱስ እያፌዙ ነበር፡፡

የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን

ወታደሮቹ በኢየሱስ እያፌዙ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ነህ ብለን አናምንም፤ ግን ከሆንህ ራስህን በማዳን ስህተታችንን አሳየን››

ከእርሱ በላይ ምልክት

‹‹ኢየሱስ መስቀል ዐናት ላይ የነበረ ጽሑፍ››

ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው

ምልክቱን ከእርሱ በላይ በማድረግ ሰዎቹ ኢየሱስ ላይ እያፌዙ ነበር፡፡ ንጉሥ ነው ብለው አያስቡም፡፡