am_tn/luk/23/29.md

2.2 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ለሕዝቡ መናገሩን አበቃ

እነሆ

ይህ የኢየሩሳሌም ሴቶች ለራሳቸው የሚያለቅሱበትን ምክንያት ያቀርባል፡፡

ጊዜ ይመጣል

‹‹በቅርቡ ጊዜ ይመጣል››

እንዲህ የምትሉበት

‹‹ሰዎች እንዲህ የሚሉበት››

መካኖች

‹‹ልጆች የሌሉዋቸው ሴቶች››

ያልተሸከሙ ማሕፀኞች… ያላጠቡ ጡቶች

ገለጻዎቹ የተሰጡት፣ ‹‹መካኖችን›› የበለጠ ለመግለጽ ነው፡፡ እነዚህ ሴቶች አልወለዱም፤ ልጆች ጡት አላጠቡም፡፡ ሁለቱንም ከመካንነት ጋር ማያያዙ ይጠቅማል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልጆች ያልወለዱ፣ ወይም ጡት ያላጠቡ መካኖች››

ከዚያም

በዚያ ጊዜ

ተራሮችን

ሐረጉን አጭር ለማድረግ ቃላት ተትተዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተራሮችን ይሉዋቸዋል››

በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆነ፣ በደረቁ ምን ያደርጉ ይሆን?

ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው በመልካሙ ጊዜ ይህን ያህል መጥፎ ነገር ካደረጉ፣ ወደ ፊት በሚመጣው ክፉ ጊዜ ደግሞ ከዚህ የከፋ ነገር እንደሚያደርጉ ሕዝቡ መገንዘብ እንዲችሉ ለመርዳት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዛፉ ደረቅ በሚሆንበት ጊዜ የበለጠ መጥፎ ነገር እንደሚያደርጉ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ››

እርጥብ ዛፍ

እርጥብ ዛፍ የመልካም ነገር ምሳሌ ነው፡፡ ቋንቋህ ተመሳሳይ ምሳሌ ካለው እዚህ ተጠቀምበት፡፡

በደረቁ

ደረቅ ዛፍ ለመቃጠል ብቻ የሚጠቅም ነገርን የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡

እነርሱ

ይህ የሚያመለክተው ሮማውያንን ወይም የአይሁድ መሪዎችን ሊሆን ይችላል፡፡ ከሁለት አንዱን ብቻ አይደለም፡፡