am_tn/luk/23/23.md

1.3 KiB

አጥብቀው ለመኑት

‹‹ሕዝቡ አጥብቀው ለመኑት››

በታላቅ ድምፅ

‹‹በጩኸት››

እርሱ እንዲሰቀል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጲላጦስ ወታደሮች ኢየሱስን እንዲሰቅሉ››

ጩኸታቸው እሺ አሰኘው

‹‹ጲላጦስ እሺ እስኪል ድረስ ሕዝቡ ጩኹ››

የጠየቁትን ለማድረግ

‹‹ሕዝቡ የጠየቁትን ለማድረግ››

የለመኑትን ፈታላቸው

ጲላጦስ በርባንን ከእስር ፈተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጲላጦስ ሕዝቡ የለመኑትን በርባንን ፈታው››

በግድያ እስር ቤት… የነበረውን

ይህ በዚያ ጊዜ በርባን የት እንደ ነበር ዳራ መረጃ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሮማውያን በግድያ አስረውት… የነበረውን››

ኢየሱስን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው

‹‹ሕዝቡ የፈለጉትን እንዲያደርጉበት ጲላጦስ ወታደሮቹ ኢየሱስን እንዲያመጣላቸው አዘዘ፡፡