am_tn/luk/23/20.md

1.2 KiB

እንደ ገና ነገራቸው

‹‹በድጋሚ ተናገራቸው›› ወይም፣ ‹‹ለሕዝቡና ለሃይማኖት መሪዎች እንደ ገና ነገራቸው››

ኢየሱስን ሊፈታው ፈልጐ

‹‹ኢየሱስን ነጻ ማድረግ ስለ ፈለገ››

ለሦስተኛ ጊዜ አላቸው

‹‹ጲላጦስ ለሦስተኛ ጊዜ እንደ ገና ለሕዝቡ አላቸው››

ይህ ሰው ምን ያደረገው አለ?

ጲላጦስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ኢየሱስ ንጹሕ መሆኑን ሕዝቡ እንዲረዱ ለማስቻል ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ ሰው ምንም ያደረገው በደል የለም››

ለሞት ፍርድ የሚያበቃ ምንም አላገኘሁበትም

‹‹ለሞት የሚያበቃው ምንም አላደረገም››

ከገረፍሁ በኋላ እፈተዋለሁ

እርሱ ንጹ በመሆኑ ሉቃስ 23፥16 ላይ ጲላጦስ ያለ ምንም ቅጣት ሊፈታው ይገባ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፣ የሕዝቡን ቁጣ ለማብረድ ኢየሱስን መቅጣት ፈለገ፡፡

እፈታዋለሁ

‹‹ነጻ እለቀዋለሁ››