am_tn/luk/23/18.md

1.1 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 19 በርባን ማን እንደ ነበር መረጃ ይሰጠናል፡፡

ሁሉም በአንድነት ጮኹ

‹‹ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ጮኹ››

ይህን ሰው አስወግደውና ፍታው

‹‹ይህን ሰው ወዲያ በለው፤ ፍታልን! ወታደሮቹ ኢየሱስን እንዲገድሉ እየጠየቁት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህን ሰው ወዲያ ብለህ ግደለው፤ ፍታው››

ፍታልን

‹‹እኛ›› የሚለው የሚያመለክተው ሕዝቡን ብቻ እንጂ፣ ጲላጦስንና ወታደሮቹን አይደለም፡፡

በርባን… ግድያ ሰው ነበር

ይህ ስለ በርባን ማንነት ሉቃስ የሚሰጠን ማስረጃ ነው፡፡

ታስሮ ነበር

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሮማውያን አስረውት ነበር››

በከተማው በማመፅ

‹‹የከተማው ሰዎች የሮም መንግሥት ላይ እንዲያምፁ ለማነሣሣት በመሞከር››