am_tn/luk/23/15.md

1.6 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ጲላጦስ ለአይሁድ መሪዎችና ለሕዝቡ መናገር ቀጥሏል፡፡

ሄሮድስም እንዲሁ

እዚህ አጭር ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያልተካተተ መረጃ መጨመር ሊጠቅም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሄሮድስም ቢሆን በደለኛ ነው ብሎ አያስብም›› ወይም፣ ‹‹ሄሮድስም ቢሆን ንጹሕ ነው ብሎ ያስባል፡፡

ሄሮድስም ቢሆን

‹‹ሄሮድስም ቢሆን ምክንያቱም›› ወይም፣ ‹‹ሄሮድስም እንዲሁ፤ ምክንያቱም እኛ እናውቃለን››

ወደ እኛ መልሶታል

‹‹ሄሮድስ ኢየሱስን ወደ እኛ መለሰው›› — ‹‹እኛ›› የሚለው ጲላጦስን፣ ወታደሮቹን፣ ካህናትና ጸሐፍትንና እንጂ፣ ጲላጦስንና እየሰሙ የነበሩን ሰዎች አያመለክትም፡፡

ለሞት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሞት ፍርድ የሚያደርስ ምንም አላደረገም››

ስለዚህ እቀጣዋለሁ

ጲላጦስ ኢየሱስ ላይ ጥፋት ባለማግኘቱ ሳይቀጣው ሊፈታው ይገባ ነበር፡፡ ይህ ዐረፍተ ነገር ትርጒሙ ውስጥ ምክንያታዊ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሕዝቡን በመፍራቱ ብቻ ንጹሕ መሆኑን የሚያውቀውን ኢየሱስን ጲላጦስ ቀጣው፡፡