am_tn/luk/23/03.md

1.2 KiB

ጲላጦስ ጠየቀው

‹‹ጲላጦስ ኢየሱስን ጠየቀው››

እንደዚያ ትላለህ

ይህም ማለት፣ 1) እንዲህ ሲል ኢየሱስ እርሱ የአይሁድ ንጉሥ መሆኑን እያመለከተ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አዎን፣ አንተ እንዳልኸው ነኝ›› ወይም፣ ‹‹አዎን፣ አንተ እንዳልኸው ነው›› ወይም 2) ኢየሱስ ይህን ሲል፣ የአይሁድ ንጉሥ በማለት የጠራው ጲላጦስ እንጂ፣ እርሱ አለመሆኑን እያመለከተ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያንን ያልኸው አንተ ራስህ ነህ››

መላው ሕዝብ

ብዙ ሕዝብ

በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም

‹‹ይህን ሰው በምንም ዐይነት በደለኛ ሆኖ አላገኘሁትም››

ሲያውክ

‹‹በመካከል ሲረብሽ››

ከገሊላ ጀምሮ፣ መላው ይሁዳ ሳይቀር እዚህ ድረስ

ይህን እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በይሁዳ ሁሉ፤ በገሊላ አሁን ደግሞ እዚህ ያውካል››