am_tn/luk/22/69.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ለሸንጐው መናገር ቀጥሏል

ከአሁን ጀምሮ

‹‹ከዚህ ቀን›› ወይም፣ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ››

የሰው ልጅ

ኢየሱስ በዚህ አባባል የሚጠቀመው ስለ ራሱ ለመናገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰው ልጅ፣ እኔ››

በእግዚአብሔር ኀይል ቀኝ ይቀመጣል

‹‹በእግዚአብሔር ቀኝ›› መቀመጥ ከእግዚአብሔር ታላቅ ሥልጣንና ክብር የመቀበል ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእግዚአብሔር ኀይል ጐን፣ በክብር ስፍራ ይቀመጣል››

የእግዚአብሔር ኀይል

‹‹ኀያል እግዚአብሔር›› እዚህ ላይ፣ ‹‹ኀይል›› የላቀ ሥልጣን ያመለክታል፡፡

ታዲያ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን?

ሸንጐው ይህን የጠየቀው የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱን በትክክል ኢየሱስ እንዲያረጋግጥ ስለ ፈለጉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታዲያ፣ እንደዚያ ስትል የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለትህ ነውን?

የእግዚአብሔር ልጅ

ይህ የኢየሱስ አስፈላጊ መጠሪያ ነው፡፡

እኔ እንደሆንሁ ትናገራላችሁ

‹‹አዎን፣ እናንተ እንዳላችሁት ነው?

ምን ምስክር ያስፈልገናል?

ጥያቄ ያቀረቡት ለአጽንዖት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሌላ ምስክር አያስፈልገንም››

ከአፉ ሰምተናል

‹‹ከአፉ›› የሚለው ከአነጋገሩ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንደሚያምን ሲናገር ሰምተነዋል››