am_tn/luk/22/56.md

1.6 KiB

በእሳቱ ብርሃን አጠገብ ተቀመጠ

እሳቱ አጠገብ ተቀመጠ፤ ብርሃኑ ፊቱ ላይ አበራ

ትኩር ብላ በመመልከት እንዲሀ አለች

‹‹ጴጥሮስን ትኩር ብላ በመመልከት ግቢው ውስጥ ለነበሩት ሰዎች እንዲህ አለች››

ይህም ሰውዬ ከእርሱ ጋር ነበረ

ሴትዮዋ ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበር ለሰዎቹ እየነገረች ነው፡፡ ምናልባትም የጴጥሮስን ስም አታውቅም፡፡

ጴጥሮስ ግን ካደ

‹‹ጴጥሮስ ግን እውነት አይደለም አለ››

ሴትዮ አላወቀውም

ጴጥሮስ የሴትዮዋን ስም አያውቅም፡፡ ‹‹ሴትዮ›› ሲል እየሰደባት አልነበረም፡፡ ሰዎች እየሰደባት እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ አንድ ሰው የማያውቃትን ሴት ሲጠራ ተቀባይነት ያለው ባሕል መጠቀም ትችላለህ፤ ወይም ቃሉን ተወው፡፡

አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ

‹‹አንተም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ ነህ››

አንተ ሰው አይደለሁም

ጴጥሮስ የሰውየውን ስም አያውቅም፡፡ ‹‹አንተ ሰው›› ሲለው እየሰደበው አልነበረም፡፡ ሰዎች እየሰደበው እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ አንድ ሰው የማያውቀውን ሰው ሲጠራ ተቀባይነት ያለው ባሕል መጠቀም ትችላለህ፤ ወይም ቃሉን ተወው፡፡